በኬንያ ባሪንጎ ካውንቲ የፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ መቆጣጠር የአከባቢዉን መሀበረሰብ የኑሮ ሁኔታን በከፍተኛ ማሻሻሉን ያሳያል

This post is also available in English (here) and Swahili (here)

የአየር ንብረት ለውጥ፣ የመሬት መበላሸትና እንደ ፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ ያሉ ወራሪ የባዕድ ዝርያዎች  በደረቅ እና ከፊል-ደረቅ አካባቢዎች ለባህላዊ የሰዎች  ኑሮ ዋና አደጋዎች ናቸው።እነዚህ ምክንያቶች በአርብቶ አደር እና በከፍል-አርብቶ አደሮች ዋና ሀብት የሆነውን የእጽዋት ባዮማስን ጨምሮ በስነ-ምህዳር አገልግሎቶች ላይ አሉታዊ ተፅእኖዎች አላቸው። በዶ/ር ሬኔ ኤሽቼን እና ባልደረቦቻቸው የተደረገ ጥናት እንደሚያመለክተው ወራሪ እንጨት የሆነዉን ፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራን በማፅዳት እና በኋላ ይህንን መሬት ወደ ሳር መሬት መመለስ ለአከባቢው ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ የገንዘብ ጥቅም ሊኖረው እና በኬንያ ባሪንጎ ካውንቲ ውስጥ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ አስተዋፅዖ አለው።

ከአራት ሀገሮች የተውጣጡ የፒኤችዲ ተማሪዎችን ያካተተ ከተለያዩ የዲሲፕሊን ዳራዎች የተውጣጡ ሳይንቲስቶችን ያካተተ ቡድን እ.ኤ.አ. በአሜሪካን ሀገር በምገኘዉ በSESYNC ሜሪላንድ ዩኒቭርስቲ በ2018 የሰመር ኢንስቲትዩት በመገኘት የሁለንተናዊ ምርምር ክህሎትን ለማመቻቸት በማኅበራዊ እና አካባቢያዊ ውህደት ውስጥ አዳዲስ ሳይንሳዊ የኮምፒዩተር እና የኮድ ችሎታዎችን የአጭር ግዜ ስልጠና ለመዉሰድ ተችሏል፡፡ የአጭር ግዜ ስልጠናዉ የተለያዩ የወደፊት የመሬት አጠቃቀም ሁኔታዎችን እንድናዳብር እና የፕሮሶፒስን ወረራ መቆጣጠር እና የሣር መሬት መልሶ ማቋቋም በአፈር ኦርጋኒክ ካርቦን ክምችት እና በአካባቢዉ መሀበረሰብ የኑሮ ሁኔታ ላይ  አንድምታዎችን እንድንገመግም አስችሎናል።

ጥናቱ በWoody Weeds ፕሮጀክት በፒኤችዲ ተማሪዎች የተሰበሰቡ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሥነ ምህዳራዊ መረጃዎች በተቀናጀ መልኩ ተጠቅመንበታል። ለምሳሌ ለፕሮሶፒስ መቆጣጠር የሚውለው የበጀት መጠንን ለመገመት ከተወገዱ ዛፎች ከምመረት የከሰል ሽያጥ ገቢ መረጃን ተጠቅመናል ። በተመሳሳይ ሁኔታ የሣር መሬት መቋቋምን እና መመስረትን ተከትሎ የአፈር ኦርጋኒክ ካርቦን ለውጥን ለመገምገም የተለያዩ የአፈር መለኪያዎች ተጠቅመናል፡፡ የተሰበሰቡ መረጃዎች ከሳተላይት መረጃ ከተገኘው የቦታ አቀማመጥ-ግልጽ የመሬት ሽፋን እና የመሬት አጠቃቀም ካርታዎች ጋር ተገናኝቷል

Eschen fig 1.1
በኬንያ ባሪንጎ ካውንቲ ከፕሮሶፒስን ወረራ መቆጣጠር እና የሣር መሬት መልሶ ማቋቋም ልግኙ የሚችሉ ፈይዳዎች

በአከባቢው ነዋሪዎች በተገለፀው አማካይ የመክፈሉ ፍላጎት የምናገኘው ውጤት እንደሚያሳየው በአንድ ዓመት ውስጥ አነስተንኛ የማይባል የፕሮሶፒስን አካባቢ ለማጽዳት የአንድ ጊዜ በጀት በቂ ነው፡፡ የተወረሩ አካባቢዎችን ወደ ሣር ምድር መለወጥ ከፍተኛ የገንዘብ ጥቅሞችን ያስገኛል። የተወሰኑት ጥቅማጥቅሞች ወዲያውኑ የተቆራረጡትን ዛፎች በመጠቀም ከሰል ማምረት ጋር የተያያዙ ሲሆኑ የረጅም ጊዜ ጥቅማጥቅሞች ግን ከተመለሱት የሣር ዝርያዎች የተገኙ ናቸው።ሣር ዝርያዎች አነስተኛ ዝናብ ስለሚፈልጉ፣ እንደ በቆሎ ወይም ባቄላ ካሉ ከአከባቢው ዋና ዋና ሰብሎች በበለጠ የአየር ንብረት ለዉጥን መቋቋም ይችላሉ፡፡ በአንዳንድ የባሪንጎ መንደሮች ቀድሞውኑ ለዘር ምርት የሚዉል ሣር ማብቀል ስልተስፋፋ አርሶ አደሮች  ሣር መሸጥ ልጀምሩ ይችላሉ፡፡ የግጦሽ ሣር ሜዳዎች መመለሳቸውም በአካባቢው ባህላዊ ኑሮን-አርብቶ አደርነትን ይደግፋል።

ስለ ወራሪ የባዕድ ዝርያዎች ስርጭት እና ጥግግት፣ ስለመቆጣጠሪያ ወጪዎች ፣ ስለገንዘብ ጥቅሞች እና ስለ የመሬት አጠቃቀም ታሪክ ዝርዝር መረጃዎችን ማዋሃድ እና ማገናኘት ትክክለኛ የመቆጣጠሪያ ዘዴዎችን ለማወቅ፤ ወጪዎችን እና ጥቅሞችን ለማሳየት የሚያገለግሉ ትክክለኛ እና ተጨባጭ የወራሪ የባዕድ ዝርያዎች አያያዝ ሁኔታዎችን ለማዘጋጀት ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ዐይነት የተቀናጀ ጥናት ለባለድርሻ አካላት ለፍላጎቶቻቸው የሚስማማውን በጣም ተገቢ እና አዋጭ የመቆጣጠሪያ ዘዴዎችን እንዲመርጡ ይረዳቸዋል ፡፡

በጥናታችን ድምዳሜ መሰራት የመሬት አስተዳደር ውሳኔዎችን ለመደገፍ በተለይም በተፈጥሮ እና በገንዘብ ሀብቶች እጥረት ባለባቸው እና የወራሪ የባዕድ ዝርያዎችን ለመቆጣጠር የሚያስፈልጉት ወጪዎች እና ጥቅሞች በአከባቢው ባለድርሻ አካላት ባልተከፋፈሉበት ሁኔታ የተቀናጀ የወራሪ የባዕድ ዝርያዎች የቁጥጥር ሁኔታዎች በስፋት ጥቅም ላይ መዋል አለባቸው።

Read the full Open Access article Prosopis juliflora management and grassland restoration in Baringo County, Kenya: Opportunities for soil carbon sequestration and local livelihoods in Journal of Applied Ecology.

2 thoughts on “በኬንያ ባሪንጎ ካውንቲ የፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ መቆጣጠር የአከባቢዉን መሀበረሰብ የኑሮ ሁኔታን በከፍተኛ ማሻሻሉን ያሳያል

Leave a comment